ባሕር ዳር: ጥር 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ሊግ ካፕ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አርሰናል ቼልሲን 3ለ2 አሸንፏል።
በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ ለአርናል ግቦችን ቤን ዋይት፣ ቪክቶር ዮኬሬስ እና ማርቲን ዙቢሜንዲ አስቆጥረዋል፡፡
ለቼልሲ ሁለቱንም ግቦች ጋርናቾ አስቆጥሯል፡፡
የአርሰናል እና የቼልሲ የመልስ ጨዋታ ከ18 ቀናት በኋላ በኤምሬትስ ይደረጋል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



