የ2026ቱ ዓለም ዋንጫ እና ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ውጥረቱ የፈጠረው ስጋት፦

0
37
ባሕር ዳር: ጥር 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የ2026 ዓለም ዋንጫን አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በጥምረት ያዘጋጁታል።
ውድድሩ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከሰኔ 11 እስከ ሐምሌ 19/2026 ድረስ ይቆያል፡፡
በጠቅላላው 104 ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲኾን 78 ጨዋታዎች ደግሞ በአሜሪካ በሚገኙ የተለያዩ ስታዲየሞች ይከናዎናሉ ተብሏል፡፡ በርካታ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶችም መሸጣቸው እየተዘገበ ነው።
የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ እስከ ታኅሣሥ ወር መጨረሻ ድረስ 150 ሚሊዮን ትኬት መሸጡን ጠቁመዋል፡፡
ይህም በኳታር ከተካሄደው የዓለም ዋንጫ ከሰባት ሚሊዮን በላይ የትኬት ብልጫ አለው ነው ያሉት፡፡
ፕሬዝዳንት ኢንፋንቲኖ አያይዘውም አሜሪካ እየተከተለች ባለው የፖለቲካ ሁኔታ እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በሚስተዋለው ውጥረት ምክንያት ደጋፊዎች ወደ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ የመሄድ ስጋት እንዳደረባቸው ነው የተናገሩት።
ሮያ ኒውስ የተሰኘው የዮርዳኖስ የመገናኛ ኩባንያ በሳምንቱ መጨረሻ ወደ 16 ሺህ 800 የሚጠጉ ሰዎች በ2026 የስታዲየም መግቢያ ትኬት ለመግዛት አቅርበውት የነበረውን ጥያቄ መሰረዛቸውን ዘግቧል፡፡
ፊፋ የስፖርት ቤተሰቡን ሥጋት ለመፍታት እና ውድድሩ በሰላም ተጀምሮ በስኬት እንዲጠናቀቅም ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይቶ መፍትሔ ለማስቀመጥ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here