ባሕር ዳር: ጥር 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሪያል ማድሪድ ከሰሞኑ አሠልጣኝ ዣቢ አሎንሶን ማሰናበቱ ይታወሳል።
የቡድኑ ፕሬዝዳንት እና ባለሀብት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ኹነኛ አሠልጣኝ እያፈላለጉ መኾናቸውን ተናግረዋል።
የእርሳቸው የመጀመሪያ ዕቅድ ደግሞ ጆሴ ሞሪንሆን ዳግም ወደ ሪያል ማድሪድ መመለስ መኾኑን ፍንጭ ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንቱ “የእኔ ሀሳብ ሞሪንሆን መመለስ ነው፤ እርሱ ሪያል ማድሪድን ቢያሠለጥን በእውነት ርካታ አገኛለሁ” ማለታቸውን አስን ጠቅሶ ያሁ ኒውስ አስነብቧል።
ሞሪንሆ ወደ ስፔን የመመለስ ፍላጎት ከሌላቸው ትልቅ ስም፣ ዝና፣ የማሠልጠን ብቃት እና ውጤታማ የኾኑትን የርገን ክሎፕ፣ የአርጀንቲናን ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ወይም በቅርቡ ቼልሲን የለቀቁት ኤንዞ ማሬስካን ለማነጋገር ዝግጁ መኾናቸውን ነው የተናገሩት።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



