ባሕር ዳር: ጥር 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ማይክል ካሪክ ማንቸስተር ዩናይትድን እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በጊዜያዊ ዋና አሠልጣኝነት ለመምራት ከስምምነት ላይ ደርሷል።
ስቲቭ ሆላንድ የካሪክ ምክትል በመኾን እንደተሰየሙ ነው የተገለጸው።
ካሪክ ቡድኑን በኀላፊነት ይዞ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚሁ ሳምንት ቅዳሜ የሚደረገውን የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ላይ ውጤት ለማምጣት የሚጫዎት ይኾናል።
ይህ ሹመት የተሰጠው ክለቡ ውጤት እያጣ ባለበት እና ሩበን አሞሪም ክለቡን በለቀቁበት ወቅት መኾኑ ለአሠልጣኙ ፈተና ነው።
ማይክል ካሪክ ከዚህ ቀደምም በዩናይትድ በጊዜያዊ አሠልጣኝነት ጥሩ ውጤት ማሳየቱ የሚታወስ ሲኾን አሁን ደግሞ ክለቡን ከተደቀነበት ችግር እንዲያወጣ ኀላፊነት ተጥሎበታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



