በማንቸስተር ዩናይትድ የተፈለጉ አሠልጣኞች

0
19

ባሕር ዳር: ጥር 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ሩበን አሞሪምን ማሰናበቱ ይታዎሳል። ክለቡም በጊዜያዊ አሠልጣኝ እየተመራ ይገኛል።

አሁን የክለቡ መሪዎች ኹነኛ አሠልጣኝ ለመቅጠር እየሠሩ ይገኛሉ።

ዛሬ በወጣ መረጃ መሠረትም ክለቡ ሦሥት ስመ ጥር አሠልጣኞችን በዕጩነት መዝግቧል።

በማንቸስተር ዩናይትድ ባለሥልጣናት እጩ ውስጥ ካሉ አሠልጣኞች መካከል ጀርመናዊ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ቶማስ ቱኽል አንደኛው ናቸው።

አሠልጣኙ ቀደም ሲል በጀርመን ቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና ባየርን ሙኒክን፣ በፈረንሳይ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን፣ በእንግሊዝ ቼልሲን አሠልጥነዋል።

አሁን በማንቸስተር ዩናይትድ ከሚፈለጉት ስመ ጥር አሠልጣኞች አንዱ መኾናቸውን ሚረር አስነብቧል።

ጣልያናዊው የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ በዓለም ቁንጮ የሚባሉ ቡድኖችን በማሠልጠን ይታወቃሉ።

ለአብነትም በጣልያን ጁቬንቱስ፣ ኤሲ ሚላን እና ናፖሊ፣ በእንግሊዝ ቼልሲ፣ በጀርመን ባየርን ሙኒክ፣ በፈረንሳይ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን፣ በስፔን ሪያል ማድሪድ ይጠቀሳሉ።

እኝህ ስመ ጥሩ አሠልጣኝ አሁን በማንቸስተር ዩናይትድ መዝገብ ውስጥ በዕጩነት ስማቸው ሰፍሯል።

ሌላው የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ናቸው በማንቸስተር ዩናይትድ እይታ ውስጥ የገቡት። አሠልጣኙ ቶትንሃምን፣ ፓሪስ ሴንት ዠርሜ እና ቼልሲ ካሠለጠኗቸው ቡድኖች መካከል ይገኙበታል።

አሠልጣኙን ማንቸስተር ዩናይትድ ከሌሎች አሠልጣኞች ጋር አወዳድሮ ለመቅጠር ስማቸውን አስፍሮታል ሲል ሚረር አስነብቧል።

በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here