ባለ ተሰጥኦ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ለማፍራት ታዳጊዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ነው።

0
12

ደብረ ማርቆስ: ጥር 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው ከ13 እስከ 15 ዓመት በኾኑ ታዳጊዎች ተኪ ብሔራዊ ቡድን መገንባትን ዓላማ ያደረገ የታዳጊዎች የምልመላ ውድድር በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር እየተካሄደ ነው።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ተስፋዬ አዕምሮ ዕድሜያቸው ከ13 እስከ15 የኾኑ ታዳጊዎችን አቅም እና የእግር ኳስ ክህሎት በመመዘን በክልል ደረጃ ለሚካሄደው ምልመላ ብቁ የኾኑ ስፖርተኞችን ለማቅረብ ውድድሩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ራሳቸውን ብሎም ሀገራቸውን የሚጠቅሙ እና በትልቅ የውድድር መድረኮች የሚሳተፉ ባለ ተሰጥኦ የእግር ኳስ ተጫዋቾችን ለማፍራት ታዳጊዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ስለመኾኑ ተናግረዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተወካይ ከንቲባ ተመስገን ተድላ በጸጥታ ችግሩ ምክንያት ተቀዛቅዞ የቆየውን ስፖርት ለማነቃቃት ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን አብራርተዋል ።

የስፖርት ዘርፉን በቅርበት በማገዝ የምልመላ ሂደቱ ውጤታማ እንዲኾን ክትትል እና ድጋፍ ይደረጋል ነው ያሉት።

የአንተነህ እግር ኳስ አካዳሚ አሠልጣኝ አንተነህ ያለው ከትምህርታቸው ጎን ለጎን መልካም ሥነ ምግባርን የተላበሱ ተተኪዎችን ለማፍራት በትኩረት እየሠሩ መኾናቸውን ነግረውናል።

በምልመላ ውድድሩ 15 ባለ ተሰጥኦ ተጫዋቾች የሚመረጡ ሲኾን ሰባት የእግር ኳስ ፕሮጀክቶች እና ሁለት የእግር ኳስ አካዳሚዎች ተሳትፈውበታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here