ባሕር ዳር: ጥር 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አርሰናል የ25 ዓመቱን እንግሊዛዊ የክሪስታል ፓላስ ተከላካይ ማርክ ጉሂን የቡድኑ አካል ለማድረግ በጥብቅ መፈለጉን አስታውቋል።
ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ በሚቀጥሉት ቀናት ማርክ ጉሂን እንደሚያስፈርመው እርግጠኛ መኾኑን ሚረር አስነብቧል።

ቶተንሃም የ19 ዓመቱን ብራዚላዊ ተከላካይ ሱዛንን ከሳንቶስ ቡድን ላይ ለማዘዋወር ከተጫዋቹ ጋር በግል ጉዳዮች ዙሪያ መስማማታቸውን ቢቢስ አስነብቧል።

ዎልቭስ እንግሊዛዊውን ወጣት ኢንተርናሽናል ማትየስ ማኔን በቡድን ስብስቡ ውስጥ ለማካተት ቁርጠኛ ስለመኾኑ የዘገቡት ሜይል እና ሚረር ናቸው።

የ26 ዓመቱ ግብጻዊ አጥቂ ኦማር ማርሙሽ በጥር ወር ከማንቸስተር ሲቲ የመልቀቅ እቅድ የለውም መባሉን ቢቢሲ ነው የዘገበው።

በሌላ የተያያዘ ዜና ማንቸስተር ሲቲ የ21 ዓመቱን ጣልያናዊ የቀኝ መስመር ተከላካይ ማይክል ካዮዴ ለማስፈረም መቋመጣቸውን አስታውቀዋል።

ሪያል ማድሪድ አንቶኒዮ ሩዲገርን በዚህ የዝውውር ወቅት በ10 ሚሊዮን ዩሮ ለመሸጥ እንደሚፈልግ አስታውቋል።
የተጫዋቹ የቀድሞ ቡድን ቼልሲ እና ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን ለማስፈረም ፍላጎት ማሳየታቸው ተዘግቧል።

አስቶንቪላ የ16 ዓመቱን ብሪያን ማጅን ከሜይንዝ ቡድን ላይ በ10 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም መስማማቱን ቢቢሲ አስነብቧል።