አጫጭር የዝውውር ወሬዎች፦

0
31
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጥር የተጫዎቾች የዝውውር ወቅት ሊጀመር ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። ይህን ተከትሎም የዝውውር ወሬዎች በስፋት መዘዋወር ጀምረዋል።
የእንግሊዙ ቦርንማውዝ የቶትንሃሙን ዌልሳዊ የፊት መስመር ተጫዋች ብሬናን ጆንሰንን ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመሩን በተመለከተ መረጃዎች እየወጡ ነው።
ክሪስታል ፓላስም ለተጫዋቹ 35 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ገንዘብ በመያዝ ተጫዋቹን ለማስፈረም ጥረት እያደረገ ነው።
ባርሴሎና አርጀንቲናዊ የቦርንማውዝ ተከላካይ ማርኮስ ሴኔሲን በዝውውር ማስፈረም ይፋዊ ፍላጎቱን አሳይቷል፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድ የ29 ዓመቱን ስኮትላንዳዊ አማካይ ስኮት ማክቶሚናይ ከጣልያኑ ናፖሊ ወደ ኦልድትራፎርድ ለመመለስ ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየቱም ተወርቷል።
ማንቸስተር ዩናይትድ፣ አርሰናል፣ ኒውካስትል ዩናይትድ እና ብሬንትፎርድ የሆፊንሃይሙን የ19 ዓመት አይቮሪኮስታዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ባዙማና ቱሬ ላይ ዓይናቸውን ጥለውበታል ሲል ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here