የኮትዲቯር እና ካሜሮን ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

0
42
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 19/2018 ዓ.ም አሚኮ) የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ሲካሄዱ በምድብ አምሥት እና ስድስት የሚገኙ ሀገራት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ዛሬ አራት ጨዋታዎች ናቸው የሚከናወኑት።
በምድብ ስድስት የሚገኙት ካሜሮን እና ኮትዲቯር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ሞዛምቢክን በማሸነፍ ሦሥት ነጥብ ማግኘት የቻለው ቡድኑ ዛሬ ከካሜሮን ጋር ጠንካራ ፉክክር ያደርጋል።
ካሜሮን ካለው በአፍሪካ የኳስ ደረጃ አኳያ በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ግጥሚያ ጋቦንን 1ለ0 በማሸነፍ ሦሥት ነጥቡን ማሳካት ቢችልም ያሳየው አቅም ግን ከግምት በታች ነው።
ምድቡን በሦሥት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው እየመሩ የሚገኙት ኮትዲቯር እና ካሜሮን በታሪካቸው 13 ጊዜ ተገናኝተው ስድስት ጊዜ ካሜሮን በማሸነፍ የበላይነት አላት። ኮትዲቯር አምስት ጊዜ አሸንፏል። ሁለት ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
በ2021 ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ባደረጓቸው ሁለት ጨዋታዎች አንድ አንድ ጊዜ በማሸነፍ እኩል ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ጨዋታውም ምሽት 5፡00 ይካሄዳል።
በሌሎች የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ኢኳቶሪያል ጊኒ ከሱዳን ምሽት 12፡ዐ0 ፣ አልጀሪያ ከቡርኪናፋሶ ምሽት 2፡30 እና ጋቦን ከሞዛምቢክ ቀን 9፡30 ይጫዎታሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here