በምርጫዎች የተከበበው ሴሜንዮ

0
51
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በዚህ ዓመት ድንቅ ብቃት እያሳዩ ካሉ ተጫዋቾች መካከል የበርንማውዙ አንቶኒ ሴሜንዮ አንዱ ነው። ይህ ተጫዋች በጥር የተጫዋቾች የዝውውር ወቅት በርንማውዝን እንደሚለቅ ፋብሪዚዮ አስነብቧል።
በርንማውዝ 65 ሚሊየን ፓውንድ ዋጋ ለተጫዋቹ ቆርጧል። ከፈላጊ ክለቦች መካከል ማንቸስተር ዩናይትድ ከተጫዋቹ ወኪል ጋር መነጋገሩ ተሰምቷል።
ሊቨርፑል ሴሜንዮን ቀደም ብሎ ሲፈልገው የነበረ ቢሆንም የኢሳክ መጎዳት ፍላጎቱ እንደገና እንዲያገረሽ አድርጎታል።
ማንቸስተር ሲቲም ሌላኛው የሴሜንዮ ፈላጊ ነው። እንደ ቢቢሲ መረጃ ከሆነም የጋርዳዮላው ቡድን የተጫዋቹን ተወካዮች ለማናገር ሩጫ ላይ ነው።
ቼልሲም ሴሜንዮን ለማግኘት ፍክክር ውስጥ ገብቷል።
የመስመር አጥቂው አንቶኒ ሴሜንዮን ለማግኘት በታላላቆቹ የእንግሊዝ ክለቦች መካከል ፉክክሩ እንዲህ ጦፏል።
በምርጫ የተከበበው ተጫዋቹ ግን የትኛውን ማሊያ እንደሚመርጥ እየተጠበቀ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here