የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ በሦስት ጨዋታዎች ይቀጥላል።

0
11
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በመክፈቻ ጨዋታው አዘጋጇ ሞሮኮን ከኮሞሮስ አገናኝቶ በባለሜዳዋ አሸናፊነት ተጠናቅቋል። ጨዋታውም 2ለ0 ኾኖ አልቋል።
ውድድሩ ዛሬም በሦስት ጨዋታዎች ይቀጥላል። ከምድብ አንድ ማሊ ከዛምቢያ ይጫወታሉ። ይህ ጨዋታ ምድቡን በበላይነት ለማጠናቀቅ ቅድመ ግምት ያገኘችው ሞሮኮን በመከተል ለመጠናቀቅ በሚደረገው ትግል ፍንጭ ሊሰጥ የሚችል ጨዋታ ነው ተብሎለታል። ጨዋታው 11:00 ላይ ይጀምራል።
ከምድብ ሁለት ደግሞ ደቡብ አፍሪካ ከአንጎላ እና ግብጽ ከዚንባብዌ ይጫወታሉ። የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን በቅርብ በተለያዩ ጊዜያት ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች ሦስቱን አሸንፏል።
ጨዋታው ምሽት 2:00 ላይ ነው የሚጀምረው። የዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ በግብጽ እና ዚምባብዌ መካከል ይደረጋል። የግብጽ ብሔራዊ ቡድን ዋንጫውን ለማንሳት ግምት ካገኙ ሀገራት መካከል አንዱ ነው። ሙሐመድ ሳላህን የያዘው ቡድኑ ጉዞውን ለማሳመር ምሽት በዚምባብዌ ይፈተናል።
ጨዋታውም 5:00 ላይ የሚካሄድ ይኾናል።
ዘጋቢ:- ሰመሐል ፍስሀ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here