ሊቨርፑል ወደ አሸናፊነት ተመልሳል።

0
18
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ምሽት ዘጠኝ ጨዋታዎች ተደርገዋል። ሊቨርፑል ከሜዳው ውጭ ከኢንተር ሚላን ጋር የተገናኘበት ጨዋታ ደግሞ ትኩረት አግኝቶ ነበር።
ጨዋታውን በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ሊቨርፑል 1ለ0 በማሸነፍ ወሳኝ ሦስት ነጥብ አግኝቷል። ዶሚኒክ ሳቦዝላይ በ88ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ግቧን ለሊቨርፑል አስቆጥሯል።
በሌሎች ጨዋታዎች፦
👉ባየር ሙኒክ ስፖርቲንግን 3ለ1
👉አታላንታ ቼልሲን 2ለ1
👉ባርሴሎና ፍራንክፈርትን በተመሳሳይ 2ለ1
👉ቶትንሃም ስላቪያ ፕራግን 3ለ0
👉ሞናኮ ጋላታሳራይን 1ለ0 አሸንፈዋል።
👉ፒኤስቪ በአትሌቲኮ ማድሪድ 2ለ3
👉ዩኔን ሴንት ጊሊዮስ በማርሴይ በተመሳሳይ 2ለ3
👉ካይራት በኦሎምፒያኮስ 1ለ0 በሜዳቸው ተሸንፈዋል።
ምሽት የተካሄዱ ዘጠኙም ጨዋታዎች ሁሉም በመሸናነፍ መጠናቀቃቸውም የምሽቱ ልዩ ክስተት ነበር።
በአስማማው አማረ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here