ባሕር ዳር: ኅዳር 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ15ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቀሪ ጨዋታ ከሜዳው ውጭ ወልቭስን የገጠመው ዩናይትድ 4ለ1 አሸንፏል። ቡርኖ ፈርናዴስ ሁለት፣ምቡሞ እና ማውንት ደግሞ ግቦችን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ዩናይትድ በ25 ነጥብ ደረጃው ስድስተኛ ሆኗል።
በአንጻሩ ወልቭስ በዘንድሮው የፕሪምየር ሊጉ ጉዞ በ15 ጨዋታዎች ሦስት ነጥብ ማስመዝገብ አልቻለም። በ13ቱ ተሸንፎ፣ በሁለቱ አቻ በመውጣት 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



