ሲቲ ሲያሸንፍ ቸልሲ ነጥብ ተጋርቷል፤ አርሰናል ደግሞ ተሸንፏል።

0
44
ባሕር ዳር: ኅዳር 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንቸስተር ሲቲ ሰንደርላንድን አሸንፏል።
ሲቲ ሰንደርላንድን ያሸነፈው 3 ለ 0 በኾነ ውጤት ነው። የሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ደግሞ ሮቢን ዳያስ፣ ፍደን እና ጋቫርዲወል አስቆጥረዋል።
ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ሊጉን በ33 ነጥብ እየመራ የሚገኘውን አርሰናል በ31 ነጥብ ተጠግቶታል።
ቸልሲ በበኩሉ ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ያለ ግብ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።
አርሰናል በበኩሉ በአስቶን ቪላ 2 ለ 1 ተሸንፏል። የአስቶን ቪላን የማሸነፊያ ግቦች ማቲ ካሽ እና ቡንዲያ አስቆጥረዋል፡፡
አርሰናልን ከሽንፈት ያላወጣችውን ብቸኛ ግብ ደግሞ ትሮሳርድ አስቆጥሯል።
የሊጉ መሪ አርሰናል በውድድር ዓመቱ ለ2ኛ ጊዜ ሽንፈትን አስተናግዷል። በተከታታይ ያለመሸነፍ ጉዞውም በአስቶን ቪላ ተገትቷል።
በሌሎች የሊጉ ጨዋታዎች ኤቨርተን ኖቲንግሀም ፎረስትን 3 ለ 0፤ ኒውካስትል በርንለይን 2 ለ 1፤ ስፐርስ ብሬንት ፎርድን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here