ባሕር ዳር: ኅዳር 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ መካሄድ ሲጀምር ባሕርዳር ከተማን ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያገናኘው ጨዋታ በባሕር ዳር ከተማ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
የባሕር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ግብ ከእረፍት መልስ መሳይ አገኘሁ አስቆጥሯል።
ሌላው በሊጉ በፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ የተካሄደው ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቅቋል።
ግቦቹን ፋሲል ከነማ በዳግም አወቀ አማካኝነት ሲያስቆጥር የወላይታ ድቻን ግብ መሳይ ሰለሞን አስቆጥሯል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



