ባሕር ዳር: ኅዳር 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ ሦሥት ነጥብ ያስመዘገበበትን ውጤት አስመዝግቧል።
ማንቸስተር ሲቲ ከሊድስ ዩናይትድ ያደረገውን ጨዋታ 3ለ2 በኾነ ውጤት አሸንፏል።
የሲቲን የማሸነፊያ ግቦችን ፎደን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጋቫርዲዎል ሌላኛዋን ግብ አስቆጥሯል።
የሊድስ ዩናይትድን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች ሊዊን እና ኑማቻ አስቆጥረዋል። የጨዋታውን ውጤት ተከትሎ ሲቲ ለጊዜውም ቢኾን በ25 ነጥብ በሊጉ ከመሪው አርሰናል በአራት ነጥብ ርቆ ሁለተኛ ደረጃ ተቀምጧል
በሊጉ ሌሎች ጨዋታዎች ብሬንት ፎርድ በርንለይን 3ለ1፤ሰንደርላንድ በርንማውዝን 3ለ2 ማሸነፍ ችለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን



