ደብረ ብርሃን ከተማ ደረጃውን ከፍ ሊያደርግ የሚችልበትን ጨዋታ ዛሬ ያደርጋል።

0
37
ባሕር ዳር: ኅዳር 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የወንዶች እግር ኳስ 21 ቡድኖችን በሁለት ምድብ ደልድሎ እያከናወነ ይገኛል።
ዛሬ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር በጅማ እና ሃዋሳ ከተሞች ቀጥሎ ይውላል።
የአማራ ክልል ተወካዩ ደብረ ብርሃን ከተማም ከሱሉልታ ክፍለ ከተማ በጅማ ስታዲየም ቀን 9፡30 ላይ ይጫወታል።
ቡድኑ እስካሁን ሦስት ጨዋታዎችን አድርጓል። በሁለት ጨዋታዎች አሸንፎ እና በአንዱ አቻ ተለያይቶ እና ሦስት የግብ ዕዳ ይዞ በአንድ ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ መጨረሻ ላይ ተቀምጧል።
ብርሃኖቹ (ደብረ ብርሃን ከተማ) ጨዋታቸውን ካሸነፉ ሦስት ደረጃዎችን የሚያሻሽሉበት በመኾኑ ብርቱ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ተጋጣሚው ሱሉልታ ክፍለ ከተማ በአንጻሩ አራት ጨዋታዎችን አድርጓል። በአንዱ አሸንፎ እና በሁለቱ አቻ ተለያይቶም አምስት ነጥብ በመያዝ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።
ቡድኑ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ወደ መሪዎች የሚጠጋ ይኾናል።
ምድብ “ለ”ን ሀላባ ከተማ፣ መንጌ ቤንሻንጉል፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና ደሴ ከተማ በቅደም ተከተል ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በድረ ገጹ አስነብቧል።
ምድብ “ሀ” ላይ ቀን 9፡30 በሃዋሳ ሰው ሠራሽ ሳር በተነጠፈለት ሜዳ ቡራዩ ከተማ ክፍለ ከተማ እና ሀረር ከተማ ይጫወታሉ።
ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here