ባሕር ዳር: ኅዳር 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኳታር አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ውድድር ፖርቹጋል አሸናፊ ኾናለች።
ከኦስትሪያን ጋር ለፍጻሜ የተገናኘችው ፖርቹጋል 1 ለ 0 በኾነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ኾናለች።
በካሊፋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አኒሲዮ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ፖርቹጋል አሸንፋ ዋንጫ አንስታለች።
48 ሀገራት በተሳተፉት እና ለ20ኛ ጊዜ በተደረገው ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ውድድር ፖርቹጋል በታሪኳ ለመጀመርያ ጊዜ ሻምፒዮን ኾናለች፡፡
ጣሊያን ብራዚልን በመለያ ምት በማሸነፍ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



