የዩሮፖ ሊግ የዛሬ ጨዋታዎች፦

0
70

ባሕር ዳር: ኅዳር 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዩሮፖ ሊግ አምስተኛ ዙር 18 ጨዋታዎች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ይደረጋሉ።

በሊጉ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ ቡድኖች ወደ መጨረሻው ዙር አላፊ ይኾናሉ።

እኛም በደረጃ ሰንጠረዡ እስከ ስምንተኛ ደረጃ የያዙ ቡድኖች የሚያደርጉት ጨዋታ ለዳሰሳ መርጠን አቅርበናል።

በሀንጋሪ ሊግ በሦስተኛነት የተቀመጠው ፈረንከቫሮስ በዮሮፖ ሊግ እስካሁን ካደረጋቸው አራት ግጥሚያዎች በአንዱም ያልተሸነፈ ጠንካራ ቡድን ነው።

ቡድኑ 10 ነጥብ በመያዝም ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ይህ ቡድን ወደ ቱርክዬ በመጓዝም በዩሮፖ ሊግ የደረጃ ሰንጠረዡ 15ኛ እንዲሁም በሀገሪቱ ሊግ በሁለተኛነት የተቀመጠውን ፊነርባቼን ይገጥማል።

ፈረንከቫሮስ መሪ ለመኾን ፊነርባቼን ደግሞ ሰባት ደረጃዎችን ለማሻሻል ጠንካራ ጨዋታ ያደርጋሉ ተብሎ ተገምቷል።

ጨዋታው 50 ሺህ ተመልካች በሚይዘው በቾባኒ ስታዲየም ምሽት 2:45 ላይ ይደረጋል።

በሌላ ጨዋታ የቡልጋሪያው ሉዶጎሬትስ ራዝግራድ ከአራት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ነው። ይህ ቡድን
የስፔኑን ሴልታ ቪጎ ያስተናግዳል።

ሴልታ ቪጎ ከአራት ጨዋታዎች በአንዱ ተሸንፎ በሦስት ጨዋታዎች አሸንፎ ዘጠኝ ነጥብ በመያዝ አራተኛ ነው።

ሴልታ ቪጎ ጨዋታውን አሸንፎ መሪ ለመኾን ብርቱ ፉክክር ያደርግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የቼኩ ቪክቶሪያ ፕለዜን የጀርመኑን ፍሪበርግን በዱሳን ስታዲየም ያስተናግዳል።

ቪክቶሪያ ፕለዜን ከአራት ጨዋታዎች በሁለቱ አሸንፎ እና በሁለቱ አቻ ተለያይቶ ስምንት ነጥብ በመያዝ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ጨዋታውን ካሸነፈ ደረጃውን ከፍ ያደርጋል።

ተጋጣሚው የጀርመኑ ፍሪበርግ ከአራት ጨዋታዎች 10 ነጥብ በመያዝ በሁለተኛነት የተቀመጠ ነው። በመኾኑም ምሽት 2:45 የሚደረገው ጨዋታ ከወዲሁ አጓጊ ኾኗል።

ሌላው ጠንካራ ጨዋታ ይደረግበታል ተብሎ የተገመተው የእስራኤሉ ማካቢ ቴላአቪቭ ከፈረንሳዩ ከኦሌይምፒክ ሊዮንስ ምሽት 5 ሰዓት በቲኤስ ሲ አሬና ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ነው።

ኦሌይምፒክ ሊዮንስ በሊጉ ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች በሦስቱ አሸንፎ ዘጠኝ ነጥብ በመያዝም ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ነጥቡን 12 በማድረስ ደረጃውን ከፍ ማድረግ ያስችለዋል።

ሌሎች ጨዋታዎችም ምሽት 2:45 ይደረጋሉ። አስቶን ቪላ ከያንግ ቦይስ፣ ፌይኑድ ከሴልቲክ፣ ሊል ከዲናሞ ዛግሬብ፣ ፓኦክ ከብራን፣ ፖርቶ ከናይስ፣ ሮማ ከ ሚቲላንድ ይደረጋሉ።

ምሽት 5ሰዓት ደግሞ ቦሎኛ ከሬድ ቡል ሳልዝበርግ፣ ጊንክ ከባሴል፣ ጎ ኤሄድ ኤግልስ ከስቱትጋርት፣ ኖቲንግሃም ፌሬስት ከማልሞ፣ ፓናቲኒኮስ ከስቱመሰግራዝ፣ ሬንጀርስ ከስፖርቲንግ ብራኛ፣ ሪያል ቢትስ ከዩትሬች፣ ሬድ ስታር ቤልግሬድ ከኤፍሲኤስ ቢ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here