ፋሲል ከነማ እና ሀዋሳ ከተማ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

0
57
ባሕር ዳር: ኅዳር 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ሲቀጥሉ አራት ጨዋታዎች በአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ከተሞች ይካሄዳሉ።
በዛሬው ጨዋታ ፋሲል ከነማ እና ሀዋሳ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። በሊጉ በስድስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በደረጃ ሠንጠረዡ በ13 ነጥብ ሁለተኛ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ እና በሊጉ ደረጃ በ12 ነጥብ አራተኛ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ዛሬ አንደኛው ሌላኛውን አሸንፎ ደረጃውን ለማሻሻል ነው ጨዋታቸውን የሚያደርጉት።
ፋሲል ከነማ ባለፈው የስድስተኛ ሳምንት ጨዋታ ላይ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ተጫውቶ ያለምንም ግብ ነጥብ ተጋርቶ የወጣበትን ጨዋታ በማሻሻል ሦሥት ነጥቡን ለማግኘት የሚጫዎት ይኾናል።
በአንጻሩ ሀዋሳ ከተማዎች በስድስተኛ ሳምንት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 በማሸነፍ የነበራቸውን ግስጋሴ ዛሬም ለማስቀጠል ይጫዎታሉ። ጨዋታውም 10፡00 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።
በሊጉ ዛሬ ሌሎችም ጨዋታዎች ሲካሄዱ መቻል ከሲዳማ ቡና 7፡00 ሰዓት ላይ፣ ሀዋሳ ስታዲየም ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ 9፡00 ሰዓት ላይ፣ ሀዋሳ ላይ ሸገር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር 12፡00 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here