ባሕር ዳር: ኅዳር 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሴካፋ ውድድር ለአምስተኛ ጊዜ እና የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል።
ይህ ጨዋታ በሁለት ምድብ ተከፍሎ ነው ሲካሄድ የቆየው። በምድብ አንድ የተደለደለችው ኢትዮጵያ ዛሬ ኬንያንን ትገጥማለች።
በዛሬው ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ቀድመው ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸውን ቢያረጋግጡም ምድቡን በበላይነት ሆኖ ለማጠናቀቅ ፍክክር ያደርጋሉ።
ሁለቱ ቡድኖች አንዱ ሌላውን በማሸነፍ ምንያክል ጥንካሬ እንዳለው ይፈታተሹበታል።
በምድብ አንድ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በሰባት ነጥብ በግብ ክፍያ በልጣ በተመሳሳይ ነጥብ ላይ ከምትገኘው ኬንያ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በመኾኑ ማን በበላይነት ምድቡን እየመራ ሊያጠናቅቅ ይችላል የሚለውን የሚመልስ ጨዋታ ነው።
ጨዋታውም 10፡00 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡
በተመሳሳይ ዛሬ ከምድባቸው የተሰናበቱት ደቡብ ሱዳን እና ሩዋንዳ የመርሐ ግብር ማሟያ ጨዋታቸውን 7፡00 ላይም ያደርጋሉ።
ከምድብ ሁለት ደግም በድሬዳዋ ስታዲየም በስድስት ነጥብ ሁለተኛ ላይ ያላችው ዩጋንዳ ከጂቡቲ ምሽት 1፡00 ላይ ሲጫዎቱ ሱዳን ከቡሩንዲ ቀን 10፡00 ላይ የሚጫወቱ ይሆናል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



