ሚላን ደርቢ ይጠበቃል።

0
48
ባሕር ዳር: ኅዳር 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጣልያን ሴሪኤ የ12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ የምንጊዜም ተፎካካሪ፣ ተቀናቃኝ የኾኑት ኢንተር ሚላን እና ኤሲ ሚላን የሚያደርጉት ጨዋታ በዓለም የስፖርት ቤተሰብ ዘንድ በጉጉት ተጠባቂ ኾኗል።
ጨዋታው በስታዲዮ ጁሴፒ ሜዛ ስታዲየም ምሽት 4 ሰዓት ከ45 ላይ ይደረጋል።
ከ75 ሺህ በላይ ተመልካም በስታዲየም ተገኝቶ ይከታተለዋል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢንተር ሚላን እስካሁን 11 ጨዋታዎችን አድርጎ በስምንቱ አሸንፏል። በሦስት ጨዋታዎች ተሸንፎ እና 24 ነጥብ በመሠብሠብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ተጋጣሚው ኤሲ ሚላን ደግሞ ከ11 ጨዋታዎች በስድስቱ አሸንፎ፣ በአራቱ አቻ ተለያይቶ፣ በአንዱ ተሸንፎ 22 ነጥብ በመያዝ አምስተኛ ላይ ይገኛል።
የኢንተር ሚላን እና ኤሲ ሚላን የነጥብ ልዩነት ሁለት ብቻ መኾኑ ጨዋታው ብርቱ ፉክክር እንደሚደረግበት ይጠቁማል።
እንደ አውሮፖ አቆጣጠር ከ2009 በኋላ ሁለቱ ኀያል ቡድኖች በ44 ጨዋታዎች ተገናኝተው ኢንተር ሚላን 22 ጨዋታዎችን በማሸነፍ የበላይነት ይዟል።
ኤሲ ሚላን በ12 ጨዋታ አሸንፏል።
በ10 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
ሁለቱ ቡድኖች አንድ ስታዲየምን በጋራ መጠቀማቸው የሁለቱን አንድዮሽ ያመላክታል።
በሌሎች የዛሬ ጨዋታዎች ቀን 8 ሰዓት ተኩል ቬሮና ከፓርማ፣ ክሬሞንስ ከሮማ 11 ሰዓት፣ ላዚዮ ከሌቼ ምሽት 2 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ሴሪኤውን ናፖሊ በመምራት ላይ ይገኛል። ኢንተር ሚላን በሁለተኛነት ሲከተል ሮማ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ይገኛል።
ጅኖዋ፣ ቬሮና እንዲኹም ፊዮሬንቲና በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ተቀምጠዋል ሲሉ ቢቢሲ ስፖርት እና ዴይሊ ሜይል ስፖርት አስነብበዋል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here