በአውሮፓ ሀገራት ትልልቅ ሊጎች የደረጃ ለውጥ የሚያስከትሉ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

0
36
ባሕር ዳር: ኅዳር 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን ላሊጋ 13ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 12፡15 በ28 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ባርሴሎና አራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው አትሌቲክ ቢልባኦ ጋር ይጫወታል።
ባርሴሎና ካሸነፈ ነጥቡን 31 በማድረስ ሪያል ማድሪድን በግብ ክፍያ በመብለጥ የመሪነቱን ቦታ ይረከባል።
በሌላ ጨዋታ ምሽት 5፡00 ላይ ቪያሪያል እና ማዮርካ ይጫወታሉ።
በጣሊያን ሴሪኤ የ12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ደግሞ በ22 ነጥብ አራተኛ ደረጃ የሚገኘው ናፖሊ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን አታላንታን ይገጥማል። ጨዋታው ምሸት 4፡ 45 ይደረጋል።
ናፖሊ ካሸነፈ መሪነቱን ከኢንተር ሚላን የሚረከብ ይኾናል።
ቦሎኛ እና ኡዴኔዜ ቀን 11፡00 የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ነው። ቦሎኛ ካሸነፈ ነጥቡን 24 በማድረስ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ይላል።
በሌሎች ጨዋታዎች ካግሊያሪ ከጄኖዋ ቀን 11፡00 እንዲሁም ፊዮሬንቲና ከጁቬንቱስ ምሽት 12፡00 የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
በፈረንሳይ ሊግ አንድ የ13ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ምሽት 1:00 ሌንስ ከስትራስቡርግ፤ ምሽት 3፡ዐዐ ደግሞ ስምንተኛ ላይ የሚገኘው ሬንስ ስድስተኛ ደረጃ ከተቀመጠው ሞናኮ ይጫወታል።
ምሽት 5፡ዐ5 ከሊጉ መሪ ማርሴይ በአንድ ነጥብ ብቻ ዝቅ ብሎ የሚገኘው ፒኤስ ጂ ከሌ. ሐቭሬ ይጫወታል።
ፒኤስጂ ካሸነፈ መሪነቱን ከማርሴል ይረከባል።
ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here