ባሕር ዳር: ኅዳር 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምሽት በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ራባት የ2025 የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት ይካሄዳል፡፡
የሊቨርፑሉ ሞሐመድ ሳላ፣ የፒኤስጂው አሽራፍ ሀኪሚ እና የጋላታሳራዩ ቪክቶር ኦሲምህን በወንዶች ዘርፍ የመጨረሻ ሦስት ዕጩ ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡
የኬፕ ቨርዴው ቡቢስታ፣ የሞሮኮው ዋሊድ ሬግራጉይ እና የሞሮኮ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሞሐመድ ኦሃቢ በአሰልጣኝ ዘርፍ የመጨረሻዎቹ ተፎካካሪዎች ኾነዋል፡፡
እንደ ካፍ ኦላይን መረጃ የዓመቱ ምርጥ ብሔራዊ ቡድን፣ ምርጥ ክለብ ምርጥ ወጣት ተጫዋች እና ሌሎችም ሽልማቶች ምሽት በራባት ይደምቃሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



