ብርቱ ፉክክር የሚደረግበት የጀርመን እና የስሎቫኪያ ጨዋታ።

0
62
ባሕር ዳር: ኅዳር 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ብርቱ ፉክክር የሚደረግባቸው የአውሮፖ ሀገራት የማጣሪያ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይውላሉ።
በምድብ አንድ የተደለደለችው ጀርመን እስካሁን ካደረገችው አምስት ጨዋታዎች አራቱን አሸንፋለች። በአንዱ ተሸንፋ 12 ነጥብ በመሠብሠብ ምድቡን እየመራች ትገኛለች።
ተጋጣሚዋ ስሎቫኪያም ከአምስት ጨዋታዎች አራቱን ድል ነስታ፣ በአንዱ ተሸንፋ 12 ነጥብ በመያዝ በጀርመን በሦስት የግብ ክፍያ ብቻ ተበልጣ በሁለተኛነት ተቀምጣለች።
በመኾኑም ጨዋታው ለዓለም ዋንጫ ተሳታፊ የሚያደርገውን የመጨረሻ ትኬት ለመቁረጥ ብርቱ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ተጠብቋል።
ጨዋታው 47ሺህ 800 ተመልካች በሚይዘው በጀርመኑ የሬድ ቡል አሬና ስታዲየም ምሽት 4:45 ይካሄዳል።
ጀርመን በደጋፊዎቿ ፊት እንደመጫወቷ የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ተሰጥቶታል።
በዚሁ ምድብ በስድስት ነጥብ ሦሥተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ሰሜን አየር ላንድ አምስት ጨዋታዎችን በመሸነፍ ያለምንም ነጥብ ግርጌ ላይ ከምትገኘው ሉግዘምበርግ ምሽት 4:45 ጨዋታዋን ታደርጋለች።
ምድብ ሰባትን በ17 ነጥብ በመምራት ላይ የምትገኘው ኔዘርላንድስ ሦሥት ነጥብ ብቻ በመያዝ ግርጌ ላይ ከተቀመጠችው ሉትኒያ ምሽት 4:45 ትጫወታለች።
ከዚሁ ምድብ በተመሳሳይ ሰዓት በ14 ነጥብ በሁለተኛነት የተቀመጠችው ፖላንድ እና አምስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ማልታ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ምድብ 12ን በ19 ነጥብ እየመራች የምትገኘው ክሮሺያ ከሞንቴኔግሮ እንዲሁም ከምድቡ በሁለተኛነት የተቀመጠችው ቼክ ሪፐብሊክ ከጅብራልተር ምሽት 4፡45 ይጫወታሉ ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here