ባሕር ዳር: ኅዳር 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ፖርቹጋል አርሜንያን 9 ለ 1 አሸንፋለች፡፡
ፖርቹጋል ከምድቧ በ13 ነጥብ ወደ 2026 ዓለም ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች።
ቡሩኖ ፈርናንዴዝ እና ጃኦ ኔቬ ሀትሪክ ሲሰሩ ጎንካሎ ራሞስ፣ ሬናቶ ቪጋ እና ኮንሴሳዎ ተጨማሪ ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል።
ኤድዋርዶ ኢስፕሪሲያን የአርሜንያን የማስተዛዘኛ ግብ አስቆጥሯል፡፡
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ስድስተኛ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎውን ያደርጋል።
ፓርቹጋል በዓለም ዋንጫው መሳተፏን ያረጋገጠች 4ተኛዋ የአውሮፓ ሀገርም መኾን ችላለች፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



