ባሕር ዳር: ኅዳር 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምድብ አራት ላይ የምትገኘው አዘርባጃን ከአምስት ጨዋታዎች በአራቱ ተሸንፋ በአንዱ አቻ ተለያይታ አንድ ነጥብ ብቻ ይዛለች።
ዛሬ በሜዳዋ ምድቡን በ13 ነጥብ የምትመራውን ፈረንሳይ ምሽት 2:00 ላይ ትጋብዛለች። ጨዋታው ለአዘርባጃን መርሐ ግብር ከማሟላት የዘለለ ውጤት አያስገኝም።
በዚሁ ምድብ በተመሳሳይ ሰዓት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው አይስላንድ ሥስተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠችው ዩክሬን ጋር ትጫወታለች።
በምድብ ስድስት ላይ የሚገኙት ሀንጋሪ ከሪፐብሊክ አየርላንድ እንዲሁም የምድቡ መሪ ፖርቹጋል ከአርሜኒያ 11:00 ሲጫዎቱ ፖርቹጋል ክሪስቲያኖ ሮናልዶን በቅጣት አታሰልፍም።
እስራኤል ከሞልዶቫ ፤ ጣልያን በሜዳዋ ከኖርዌይ ከምድብ ዘጠኝ ምሽት 4:45 የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
በምድብ 11 አልባኒያ ከእንግሊዝ እንዲሁም ሰርቢያ ከላቲቪያ ምሽት 2:00 ላይ ይጫወታሉ ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



