ስፔን የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋን ለማረጋገጥ ጫፍ ደርሳለች።

0
51
ባሕር ዳር: ኅዳር 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች እየተካሄዱ ነው።
ምድብ አምስትን እየመራች የምትገኘው ስፔን ከጆርጂያ ተጫወታ 4ለ0 አሸንፋለች። ነጥቧን 15 በማድረስ ሁለተኛ ላይ ከምትገኘው ቱርክየ በሦስት ነጥብ ከፍ ብላለች።
በዚሁ ምድብ ቱርክየ ቡልጋሪያን 2ለ0 በማሸነፍ ሁለተኛ ላይ ናት። የቀረው የምድብ ጨዋታ አንድ ነው።
በመጨረሻው ጨዋታ ቱርክየ ከስፔን ምድቡን በልጣ ለመጨረስ የራሷን ጨዋታ ከማሸነፍ በተጨማሪ የስፔንን በሰፊ የግብ ልዩነት መሸነፍ ትጠብቃለች። ይህም የስፔንን የማለፍ ዕድል የተቃረበ ያደርገዋል።
ምድብ 10 ላይ የምትገኘው ቤልጄም ከካዛኪስታን ያደረገችውን ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቅቋል። ቤልጀም ጨዋታውን ብታሸንፍ ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ማለፏን ታረጋግጥ ነበር።
በሌሎች ጨዋታዎች ኦስትሪያ ቆጽሮስን 2ለ0፤ ዌልስ ሊችተንስቲን 1ለ0፣ ስዊዘርላንድ ስዊዲንን 4ለ1፣ ኮሶቮ ስሎቫኒያን 2ለ0፣ ግሪክ ስኮትላንድን 3ለ2 እና ቦስኒያ ሮማኒያን 3ለ1 ረትተዋል። ቤላሩስ ከዴንማርክን ደግሞ 2ለ2 አቻ ተለያይተዋል።
በዋሴ ባየ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here