ባሕር ዳር: ኅዳር 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ዛሬ ጀምሯል። ዛሬ በተካሄደው ጨዋታም ኢትዮጵያ ሩዋንዳን አሸንፋለች።
ኢትዮጵያ ሩዋንዳን ያሸነፈችው 2ለ0 በኾነ ውጤት ነው።
የማሸነፊያ ግቦቹን ከእረፍት በፊት ዳዊት ካሳ እና ሁዜፋ ሻፊ አስቆጥረዋል።
ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ የሴካፋ ውድድር ላይ 10 የአፍሪካ ሀገራት እየተሳተፉ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



