የአውሮፓ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች

0
36
ባሕር ዳር: ኅዳር 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሀገራት ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ዛሬ ወሳኝ የማጣሪያ ጨዋታዎችን በተለያዩ ከተሞች ያደርጋሉ።
ምድብ ሁለትን በ10 ነጥብ እና በዘጠኝ ንጹሕ የግብ ክፍያ እየመራች የምትገኘው ስዊዘርላንድ በአንድ ነጥብ ግርጌ ላይ ከተቀመጠችው ስዊድን ጋር ምሽት 4:45 ትጫወታለች።
በሌላ የምድብ ሁለት ጨዋታ ከአራት ጨዋታዎች ሦስት ነጥብ የያዘችው ስሎቫኒያ እና በሰባት ነጥብ እና በአንድ የግብ ዕዳ ከምድቡ በሁለተኛነት ከምትገኘው ኮሶቮ ጋር ምሽት 4:45 ጨዋታቸውን ያደረጋሉ።
በ10 ነጥብ ምድብ ሦስትን የምትመራው ዴንማርክ እስካሁን ያደረገቻቸውን አራት ጨዋታዎች ከተሸነፈችው ቤላሩስ ጋር ትጫወታለች። ጨዋታው ምሽት 4:45 ላይ የሚካሄድ ይኾናል።
በሌላ የምሽት ጨዋታ 2:45 ላይ 10 ነጥብ ብትይዝም በስድስት የግብ ክፍያ በዴንማርክ የተበለጠችው ስኮትላንድ ወደ ግሪክ አምርታ ትገጥማለች።
በምድብ አምስት ጆርጅያ ከስፔን፣ ተርክዬ ከቡልጋሪያ ምሽት 2:00 ላይ ይጫወታሉ። በጨዋታው ስፔን ድል አድርጋ ተርክዬ ነጥብ ከጣለች ስፔን በቀጥታ አላፊ ትኾናለች።
በምድብ ስምንት ቆጵሮስ ከኦስትሪያ ምሽት 2:00፤ ቦሲኒያ ሄርዝጎቪኒያ ከሩማኒያ ምሽት 4:45 ላይ ይጫወታሉ።
ምድብ 10 ላይ ካዛኪስታን ከቤልጀየም ቀን11:00 ላይ የሚጫወቱ ይኾናል። ቤልጀየም ካሸነፈች አላፊ ትኾናለች። በዚሁ ምድብ ሌችስታይን ከዌልስ ምሽት 2:00 ላይ ይጫወታሉ ሲል ቢቢሲ በድረ ገጹ አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here