ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 05/2017 ዓ.ም(አሚኮ) ዘቴሌግራፍ እንደዘገበው ሴኔጋላዊው አጥቂ ኒኮላስ ጃክሰን በክረምቱ የዝውውር ወቅት ቼልሲን ለቆ ከወጣ ወደ ኒውካስትል ዩናይትድ ማምራት እንደሚመርጥ ተገልጿል።

ቼልሲ እና አርቢ ሌይፕዝሽ ሆላንዳዊውን አማካኝ ዣቪ ሲሞንስን ከፈረንሳዩ አጥቂ ክሪስቶፈር ንኩንኩ ጋር ለመለዋወጥ እየተነጋገሩ ነው ሲል ስካይ ስፖርት ጽፏል። ንኩንኩ ወደ ቀድሞ ክለቡ መመለስ የሚችልበት ሂደት ላይ መኾኑ ተዘግቧል፡፡

ሊቨርፑል የኒውካስትሉን አሌክሳንደር ኢሳክ ለማስፈረም ካልቻለ ዮአን ዊሳን ከብሬንትፎርድ ለማስፈረም እያሰበ ነው ሲል ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡

ኮሎ ሙአኒ ከኒውካስትል ይልቅ ጁቬንቱስን መቀላቀል እንደሚመርጥ መናገሩን ቢልድ ኢን ጀርመን አስነብቧል።

ማንቸስተር ዩናይትድ የኤቨርተንን የቀድሞ አጥቂ ዶሚኒክ ካልቨርት-ሌዊንን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም እያሰበ ነው።

የሳዑዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር የተባለው የባየር ሙኒኩን ፈረንሳዊ አጥቂ ኪንግስሊ ኮማን ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል ሲል የዘገበው ቶክ ስፖርት ነው።

ጃክ ግልሪሽ ከኤቨርተን ጋር ተስማምቷል። በማንቸስተር ሲቲ ቤት ቦታ እንደሌለው የተነገረው ጃክ ግልሪሽ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቆይቷል። ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንዳስነበበው ተጨዋቹ ለኤቨርተን ለመጫወት ተስማምቷል።

ቶተነሀም ብራዚላዊውን የማንቸስተር ሲቲ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሳቫኒሆን ለማስፈረም እየተነጋገረ እንደሚገኝ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ የ21 ዓመቱን ተጫዋች ለማዛወር ማንቸስተር ሲቲ 50 ሚሊዮን ዩሮ ጠይቋል፡፡

የኢሲሚላኑ ተከላካይ ማሊክ ሶ ወደ ኒውካስትል ለመዛወር ተስማምቷል። ተጫዋቹን ለማስፈረም 34 ነጥብ 62 ዩሮ ተከፍሎበታል፡፡