ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 👉አርሰናል የተጓተተበትን የቪክቶር ዮኬሬሽን ዝውውር ጨርሷል። በፋብሪዚዮ መረጃ መሠረት ዮኬሬሽ ከአሰልቺ የዝውውር ሂደት በኋላ ለአምስት ዓመታት ለአርሰናል ለመጫወት የዝውውር ሂደቱ ተጠናቅቋል።
👉ማንቸስተር ዩናይትድ ኢሚላኖ ማርቲኔዝን እየፈለገ ነው። ዩናይትድ ተጫዋቹን ከአስቶን ቪላ በውሰት ማስፈረም ቢፈልግም ውድቅ ተደርጎበታል። ቪላ አርጀንቲናዊውን ግብ ጠባቂ በ40ሚሊዮን ፓውንድ መሸጥ እንደሚፈልግ ሜል ጽፏል።
👉ሊቨርፑል እና ቶትንሃም ማርክ ጉሂን ለማስፈረም እየተፎካከሩ ነው። እንደ ስታር ዘገባ እንግሊዛዊ የክሪስቲያል ፓላስ ተከላካይ በአርኔ ስሎቱ ሊቨርፑል በጥብቅ የሚፈለግ ሲኾን አኹን ቶትንሃም ፉክክር ውስጥ ገብቷል።
👉ዘሰን ደግሞ ኒኮላስ ጃክሰን ከጣሊያን ክለቦች የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል ብሏል። አሲሚላን እና ናፖሊ የሴኔጋላዊው አጥቂ ፈላጊዎች ናቸው። ጃክሰን የእነዚህን ክለቦች ጥያቄ አለመቀበል ለማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን ለማግኘት ጥሩ ይኾንለታልም ተብሏል።
👉አሊሃንድሮ ጋርናቾ በቼልሲ፣ ቶትንሃም እና አስቶን ቪላ ክትትል ውስጥ ነው። በቴሌግራፍ መረጃ መሰረት ክለቦቹ ተጫዋቹን ለማስፈረም እስከ 40ሚ ፓውንድ ለመክፈል ፈቃደኛ ናቸው።
👉ቼልሲ ዣቪ ሲሞንስን የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው የቴሌግራፍ መረጃ ያሳያል። ሲሞንስ አርቢ ሊፕዚንግን እንደ ሚለቅ ይጠበቃል። ቼልሲ ተጫዋቹን የማስፈረም ፍላጎት አሳይቷል። ኔዘርላንዳዊውን ተጫዋች ለማግኘት ግን ተጫዋቾችን መሸጥ እንደሚፈልግም ተገልጿል።
👉ማንቸስተር ዩናይትድ እና ማንቸስተር ሲቲ የዴንማርኩን አማካይ ሞርቲን ሁልማንድን ለማዛወር እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ኤ ቦላ እንዳስነበበው ተጫዋቹ ከሰፖርቲንግ ሊዝበን የመልቀቅ ፍላጎት አለው።
👉እንደ ካልችዮ መርካቶ ዘገባ ፍሬድሪኮ ኬዛ በጁቬንቱስ፣ አሲሚላን፣ ኢንተር ሚላን እና ሮማ እየተፈለገ ነው።
👉ጃንሉጅ ዶናሮማን ለማግኘት ጋላታሳራይ እየተንቀሳቀሰ መኾኑ የጻፈው ደግሞ ቱቶ መርካቶ ዌብ ነው። ተጫዋቹ በፒኤስጂ የአንድ ዓመት ውል ብቻ ቢቀረውም እስካኹን ውሉን አላራዘመም።
በአስማማው አማረ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!