አርሰናል የተጫዋቹን ውል አራዘመ፡፡

0
229

ባሕር ዳር: ግንቦት 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አርሰናል የ32 ዓመቱን አማካይ ተጫዋች ጆርጊንኾ በኤምሬትስ የሚያቆየውን የአንድ ዓመት ውል ማራዘሙን አስታውቋል።ተጫዋቹ በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ደመወዝ በጥር 2023 የዝውውር ወቅት ቼልሲን ለቅቆ ለአርሰናል የአንድ ዓመት ከስድስት ወር ውል መፈረሙን ቢቢሲ አስታውሷል።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለቡድኑ ጥሩ ግልጋሎት እየሰጠ ይገኛልም ብሏል፡፡ አሠልጣኝ አርቴታ “ጆርጊንኾ ከእኛ ጋር ውሉን በማራዘሙ በጣም ደስ ብሎናል፡፡ እሱ ጨዋታ በመምራት ክህሎት እና በአጨዋዎት ችሎታው ለቡድናችን አስፈላጊ ተጫዋች ነው” ሲል ተናግሯል፡፡

ጆርጊንኾ በዚህ የውድድር ዘመን በ23 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ተሰልፎ አርሰናል በ17 ጨዋታዎች አሸንፏል፤ ጆርጊንኾ በተሰለፈበት ጨዋታ መድፈኞቹ የተሸነፉት በሁለቱ ጨዋታዎች ብቻ ነው ፡፡ በአራት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይቷል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here