ባሕር ዳር: ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አሠልጣኙ አስቶን ቪላን እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2022 ነው የተረከቡት። ቡድኑን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሻሻልም በያዝነው የውድድር ዘመን የሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ ሊያደርጉት ጫፍ ደርሰዋል።
የኢምሬ ኮንትራት ሊጠናቀቅ ሁለት ዓመት ቀረቶታል። ነገር ግን በቪላ ፓርክ ባከናወኑት አስደናቂ ሥራ የቡድኑ ባለቤቶች አሠልጣኙ ተጨማሪ ዓመታትን እንዲቁዩ ፍላጎት ነበራቸው። ይህ ፍላጎታቸው እውን ኾኖ አሠልጣኙ እስከ 2027 ለመቆየት መስማማታቸውን ዴይሊ ሜይል ዘግቧል። ኡናይ ኢምሬ ከ2004 ጀምሮ ቫሌንሲያ፣ ስፓርታክ ሞስኮ፣ ፓሪስ ሴንት ዥርሜ፣ አርሰናል እና ሌሎችን ስመ ጥር ቡድኖችን ማሠልጠናቸውን ይታወሳል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!