የጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የግማሽ ማራቶን ውድድር በጃፖኗ ከተማ ተካሄደ።

0
372

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የሚሆን ከ 1600 በላይ ሯጮች የተሳተፉበት የግማሽ ማራቶን ውድድር በጃፓን ኢባራኪ ግዛት ካሳማ ከተማ ተካሂዷል።

በጃፓን የኢፌዴሪ አምባሳደር ዳባ ደበሌ የግማሽ ማራቶን ውድድር ያስጀመሩ ሲሆን መሰል ወድድሮች ረጅም ዘመናት ያስቆጠረውን የሁለቱን አገራት መልካም ግንኙነት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ይበልጥ አጠናክሮና አስተሳስሮ ለማስቀጠል ሚናው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።

የጃፖን መንግስት ይህን ውድድር በማዘጋጀቱና የጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ በማድረጉም ምስጋና አቅርበዋል።

የካሳማ ከተማ ከንቲባ ሺንጁ ያማጉቺ በበኩላቸው፤ የከተማው አስተዳደር ከኤምባሲው ጋር እየሰራ ያለውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ከከተማዋ አስተዳደር የተውጣጣ ልዑክ በመምራት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙና ከኢትዮጵያ ከተሞች ጋር ግንኙነት በመመስስረት በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here