ባሕር ዳር: ሚያዚያ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ16ኛ እስከ 22ኛ ሳምንት በድሬዳዋ ከተማ ድሬዳዋ ስታዲየም እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።
‘በኢትዮጵያ ዋንጫ’ ጨዋታዎች ምክንያት ሊጉ ከተቋረጠ በኋላ ሲመለስ ከዚህ በፊት በወጣው መርሐግብር ይቀጥላል። ከ23ኛ ሳምንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በሀዋሳ ከተማ ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማኅበር መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!