በ11 ዓመታት የእግር ኳስ ህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የውስጥ ሊግ ዋንጫ ያጣው ኪንግስሊ ኮማን።

0
318

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፈረንሳዊ ተጫዋች ኮማን በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ተጫውቷል። ገና 27 ዓመቱ ቢኾንም በርካታ ድሎችን ማሳካትም ችሏል። የተለያዩ ሀገራት ሊጎችን እና ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ ችሏል። በ16 ዓመቱ ለፈረንሳዩ ፒኤስጅ ዋናው ቡድን መሰለፍ የጀመረው ኮማን ለሁለት ዓመታት በፓሪስ ሲቆይ ሁለቱንም ዓመት የፈረንሳይ ሊግ አንድን አሸንፏል።

በ2015 ወደ ጣሊያን በማምራት ለጁቬንቱስ ፈርሟል። በቱሪን ለሁለት ዓመታት ሲጫወት በሁሉም አጋጣሚዎች በሴሪኤ ዋንጫ ደምቋል። ቀጣዩ የኪንግስሊ ኮማን ማረፊያ አሁን እየተጫወተበት ያለው ባየርሙኒክ ነው። ከ2016 ጀምሮ በጀርሙኑ ክለብ በቆየባቸው ዓመታት ሁሉ የቦንደስሊጋ ዋንጫውን አንስቷል።

ዘንድሮ ግን ባየርሊቨርኩሰን የቦንደስሊጋ ዋንጫውን የግሉ አድርጓል። ይሄ የባየርሙኒክን የበላይነት ከመግታቱ በተጨማሪ ኮማን በእግር ኳስ ህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከውስጥ ሊግ ድል ውጭ የኾነ ዓመት እንዲያሳልፍ አድርጎታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here