ባሕር ዳር: መጋቢት 27/2026 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለም አቀፍ ስፖርት ለሰላም እና ለልማት በሚል መሪ መልእክት በደሴ ከተማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴው በሁሉም ትምህርት ቤቶች ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን በከተማው ውስጥ የሚገኙ የስፖርት ማሠልጠኛ ኢንስትራክተሮች እያሠሩ ነው፡፡
በሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአካል ብቃት ሲሠሩ የደሴ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያነጋገራቸው ተማሪ አርሴማ መስፍን እና ናሆም ተፈራ የስፖርታዊ እንቅስቃሴው በአካልም በዕምሮም የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል፡፡ ወጣቱ ከሱስ እና ድብርት ለመራቅ ስፖርትን ቢያዘወትር ጥሩ መኾኑን ነው የተናገሩት። ተማሪዎቹ ስፖርት ለሰላም እና ለልማት ያለው ፋይዳ ትልቅ ስለመኾኑም ነው ያስረዱት፡፡
በትምህርት ቤት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መካሄዱ የተማሪዎችን ትምህርት የመቀበል እና የማሰብ ችሎታቸውን ከማዳበር ባሻገር የመማር ማስተማር ሥራውን የተሻለ ያደርጋልም ሲሉ ነው ያብራሩት፡፡ በዕለቱም በሁሉም ትምህርት ቤት ተመሳሳይ የአካል ብቃት ስፖርት እንቅስቃሴ ተካሂዷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!