ባሕር ዳር ከተማ ከወልቂጤ የሚያደርጉት ጨዋታ ተራዘመ።

0
313

ባሕር ዳር: መጋቢት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በ 2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በወጣው መርሐ ግብር መሰረት መጋቢት 21/2016 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ባሕር ዳር ከተማ ከወልቂጤ ከተማ እንደሚጫወቱ ቀጠሮ ተይዞ ነበር።

ነገር ግን የ2015 የሊጉ እጩ ኮከብ ተጫዋች ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባሕር ዳር ከተማ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፍት ምክንያት ጨዋታው ላልተወሰን ጊዜ መራዘሙን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር አሳውቋል። ጨዋታው የሚካሄድበት መርሐ ግብር በቀጣይ እንደሚገለጽም ማኅበሩ አሳውቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here