የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አምበል ሮይ ኪን ማንቸስተር ሲቲ እያጋጠመው ላለው የውጤት መዋዠቅ የሮድሪ መልቀቅ ትልቅ ሚና እንዳለው ገለጸ።
ሰዎች የሮድሪን ከክለቡ መልቀቅ አቅልለው እንደተመለከቱት የተናገረው ሮይ ኪን፣ አንዳንድ ጊዜ የተጫዋቾችን ትክክለኛ ዋጋ እና ክብደት መረዳት የሚጀመረው ክለቡን ከለቀቁ በኋላ መኾኑን አስገንዝቧል።
ሮድሪ ለማንቸስተር ሲቲ እጅግ ወሳኝ ተጫዋች እንደነበር ያስታወሰው ኪን፣ በአሁኑ ወቅትም ለስፔን ብሔራዊ ቡድን ትልቅ አቅም መኾኑን አክሎ ገልጿል።
#አሚኮ #ስፖርት
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_20_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



