“በገጠመኝ ጉዳት ያየሁት የሕዝብ ፍቅር የዓለም ክብረ ወሰንን አሻሽዬ ከማገኘው ክብር የበለጠ ነው” አትሌት ትዕግሥት አሰፋ

0
33

የ2026 የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በውድድሩ ላይ በገጠማት ጉዳት ምክንያት ስታደርገው የነበረውን ሕክምና አጠናቅቃ በመልካም ጤንነት ወደ ሀገሯ ተመልሳለች።

‎አትሌቷ ዛሬ ማለዳ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትደርስ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት የጀግና አቀባበል ተደርጎላታል።

‎ጀግናዋ አትሌት ትዕግሥት ከደማቁ አቀባበል በኋላ ባስተላለፈችው መልዕክት የተደረገላት አቀባበል በቀጣይ የተሻለ ውጤት እንድታስመዘግብ ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሚኾናት ገልጻለች።

‎አትሌቷ በርሊን ላይ የገጠማት ጉዳት ያልጠበቀችውን የሕዝብ ፍቅርን እንዳሳያት ገልጻ፣ “የተሰጠኝ ፍቅር ክብረ ወሰኑን አሻሽዬ ከማገኘው አድናቆት እና ዝና የበለጠ ኾኖ በማግኘቴ እጅግ ተደስቻለሁ” ብላለች።

‎አትሌቷ በፍጥነት ወደ ጤንነቷ እንድትመለስ ላገዟት ሁሉ ምሥጋናዋን አቅርባ፣ ከደረሰባት ጉዳት ሙሉ በሙሉ አገግማ ወድቆ የመነሳት ተምሳሌት ለመኾን እንደምትጥር ገልጻለች።

#አሚኮ #ስፖርት

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_20_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here