“‎በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ ውስጥ ከፀጥታ ተቋማት የተገኙ አትሌቶች ሚና ከፍተኛ ነው” በወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ መክዩ መሀመድ

0
29

የኢትዮጵያ አየር ኀይል 91ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የቢሾፍቱ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዛሬ ተካሂዷል።
‎
‎የኢትዮጵያ አየር ኀይል 91ኛ ዓመት የምስረታ በዓል
‎አየር ኀይላችን መመኪያችን በሚል መሪ መልዕክት እየተከበረ ሲኾን የመርሐግብሩ አካል የኾነው የ10ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ተካሂዷል።
‎
‎የኢትዮጵያ አየር ኀይል 91ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተካሄደው 2ኛው የቢሾፍቱ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድርም በወንዶች አትሌት ቢኒያም መላክ በሴቶች ቢኪሌ አምበሱ አሸንፈዋል።
‎
‎በውድድሩ ላይ የተገኙት በወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ መክዩ መሀመድ በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ ውስጥ ከፀጥታ ተቋማት የተገኙ አትሌቶች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።
‎
‎በተለይ የኢትዮጵያ አየር ኀይል በሀገራችን ስፖርት ታሪክ ውስጥ ያለው ሚና ከፍተኛ መኾኑን በመጥቀስ አየር ኀይል እንደነ ምሩፅ ይፍጠር አይነት አትሌቶች የተገኙበት መኾኑን አስታውሰዋል።
‎
‎አሸናፊ ሀገር ለመፍጠር በሚደረገው ዕቅድ ውስጥ አየር ኀይልን ጨምሮ የፀጥታ ተቋማት በስፖርቱ ዘርፍ ያላቸውን ሚና ለማጉላት ወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ የደርጋልም ብለዋል።
‎
‎የኢትዮጵያ አየር ኀይል 91ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተካሄደው የቢሾፍቱ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. አየር ኀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በተገኙበት ዛሬ የተካሄደ ሲኾን የአየር ኀይሉ የምስረታ ክብረ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች መካሄዱን ይቀጥላል።

በባዘዘው መኮንን

#አሚኮ #ስፖርት

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_20_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here