በ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ በወንዶች አትሌት ቢኒያም መላክ እና በሴቶች አትሌት አዳኑ ሂርፖ አሸነፉ።

0
31

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ያዘጋጀው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ለሁለተኛ ጊዜ “አየር ኀይላችን መመኪያችን” በሚል መሪ መልዕክት በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዶ ተጠናቅቋል።

አንደኛ ለወጡት አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ500 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቷል።

በምርጥ አሠልጣኞች ዘርፍ በወንዶች ሁሴን ሼቦ ከሸገር ሲቲ፣ በሴቶች ተስፋዬ ነዳሳ ከሸገር ሲቲ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

አሸናፊ አትሌቶች የሀገር አለኝታ በኾነው የአየር ኀይል የጎዳና ላይ ሩጫ በመሳተፋቸው እና በማሸነፋቸው ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

በባዘዘው መኮንን

#አሚኮ #ስፖርት

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_20_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here