የአውሮፓ ዋንጫ ቀሪ ተሳታፊዎችን ለመለየት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ።

0
442

ባሕር ዳር: መጋቢት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ2024ቱ የአውሮፓ ዋንጫ በጀርመን አስተናጋጅነት የፊታችን ሰኔ ይካሄዳል። አስካኹን 20 ሀገራት በውድድሩ የሚያሳትፋቸውን ውጤት አስመዝግበው ለጀርመኑ ጉዞ እየተሰናዱ ነው። በአውሮፓ ዋንጫው 24 ሀገራት የሚሳተፍ ሲኾን፣ አዘጋጇ ጀርመን በቀጥታ የውድድሩ ተሳታፊ ናት። ቀሪ ሦስት ሀገራት ደግሞ ቀድመው ያለፉ 20 ሀገራትን እና ጀርመንን የሚቀላቀሉ ይኾናል።

እነዚህ ቀሪ ተሳታፊ ቡድኖች በጥሎ ማለፍ ጨዋታ በሚያስመዘግቡት ውጤት ይለያሉ። የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎችም ዛሬ ይከናወናሉ። ፓላንድ ከኢስትኒያ፣ ዌልስ ከፊንላንድ፣ ቦሲኒያ ሄርዚጎቢኒያ ከዩክሬን፣ እስራኤል ከአይስላንድ፣ ጆርጅያ ከሉክዘንበርግ እና ግሪክ ከካዛኪስታን ይጫወታሉ።

የመልስ ጨዋታዎች በተመመሳሳይ ከቀናት በኋላ የሚካሄዱ ሲኾን በደርሶ መልስ ጨዋታ በድምር የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግብ ቡድን የጀርመን ጉዞውን የሚያረጋግጥ ይኾናል።

በአስማማው አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here