ኢትዮጵያውያን ዋናተኞች ድል አልቀናቸውም፡፡

0
17

በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ እየተከናወነ የሚገኘው የ2026 የአለም ወጣቶች ኦሎምፒክ ቀጥሏል፡፡ ትናንት በተለያዩ ዘርፎች ውድድሮች ተደርገዋል።በሴቶች 50 ሜትር ጀርባ ቀዘፋ ሳምራዊት ደምሌ ፣ በ50 ሜትር ደረት ቀዘፋ ኢልሀም ኑር ተሳተፈዋል፡፡ድል ግን አልቀናቸውም፡፡ሳምራዊት ደምሌ በ50 ሜትር ነጻ ቀዘፋ 32 ሰከንድ ከ11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰአት በምድቧ መጨረሻ አጠናቃለች፡፡ በ50 ሜትር ቢራቢሮ ውሃ ዋና ዘርፍና ጀርባ ቀዘፋም የተሳተፈችው ሳምራዊት ጥሩ ሰአት በማስመዝገብ አጠናቃለች፡፡በሴቶች 100 ሜትር ቢራቢሮ ኢትዮጵያን የወከለችው ኢልሀም ኑር ስትሆን የምድቧ ግርጌ ላይ 1 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ ከ17 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰአት ጨርሳለች፡፡ በተጨማሪም በተመሳሳይ ርቀት በደረት ቀዘፋ ከ 3 ተወዳዳሪዎች 2ተኛ በመውጣት የተሻለ ሰአት አስመዝግባለች፡፡ 50 ሜትር ደረት ቀዘፋም ዋናተኛዋ የተሳተፈችበት ነው፡፡ዳግም ኪሮስ በወንዶች 50 ሜትር ነጻ ቀዘፋ በምድቡ 4ተኛ ሆኖ ሲጨርስ 27 ሰከንድ ከ17 ሰከንድ በማስመዝገብ ነው፡፡ በ100 ሜትር ቢራቢሮ ከምድቡ 6ተኛ ሆኖ ሲጨርስ በተመሳሳይ በ200 ሜትር ድብልቅ ውሃ ዋና ተወዳድሮ ከውድድሩ ውጪ እንዲሆን ተደርጓል፡፡በጸሎት ሀፍቱ በወንዶች 100 ሜትር ደረት ቀዘፋ በ1፡25.63 4ተኛ ገብቷል፡፡ በተመሳሳይ በ100 ሜትር ነጻ ቀዘፋ 3ተኛ ሆኖ ሲጨርስ በ100 ሜትር ጀርባ ቀዘፋ 4ተኛ ሆኖ ጨርሷል፡፡ታዳጊዎቹ ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት ወደ ፍጻሜ ማለፍ አልቻሉም፡፡ጥቅምት 23 የጀመረው የውሃ ዋና ውድድር ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲሆን ኢትዮጵያውያኖቹ ታዳጊዎች ውድድራቸውን ትናንት ባደረጓቸው ውድድሮች አጠናቀዋል፡፡ከዚህ በኋላም ኢትዮጰያውያን ተሳታፊዎች በአትሌቲክስ በብስክሌትና በቴኳንዶ ከጥቅምት 29 ጀምሮ ውድድራቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

ሐናማርያም መስፍን

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_27_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here