አጫጭር ስፖርታዊ መረጃዎች፦

0
19

👉የማንቼስተር ዩናይትዱ የ16 ዓመቱ ድንቅ ታዳጊ ጄጄ ጋብሬል ከክለቡ ለመልቀቅ የወሰነ ሲኾን ፍላጎት ካሳዩት ክለቦች በሙሉ ምርጫው ሪያል ማድሪድ መኾኑን አሳውቋል። እንደ ባርሴሎና፣ ባየርን ሙኒክ እና ፒኤስጂ ያሉ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች እሱን ለማስፈረም ቢፈልጉም፣ ጋብሬል ግን በቃል ደረጃ ስምምነት ላይ የደረሰው ከሪያል ማድሪድ ጋር ነው ተብሏል።ዩናይትድ ታዳጊውን ለማስቀረት ቢሞክርም፣ ከክለቡ ለመልቀቅ ባቀረበው ጥያቄ ምክንያት በጥር የዝውውር መስኮት በነፃ ዝውውር ወደ ስፔኑ ክለብ ያመራል ተብሎ ይጠበቃል።👉ሪዮ ፈርዲናንድ «ማንችስተር ዩናይትድ ኤዝሪ ኮንሳን ማስፈረም ነበረበት፤ እርሱ ምርጥ ተጫዋች ነው» ሲል ወቀሰ።የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካይ ሪዮ ፈርዲናንድ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከአስቶንቪላ ወደ አርሰናል በ55 ሚሊዮን ፓውንድ ያመራውን ኤዝሪ ኮንሳን አድናንቋል።ፈርዲናንድ ማንችስተር ዩናይትድ በተለይም የኋላ ክፍል ክፍተቱን ለመድፈን ኮንሳን አለማስፈረሙ ትልቅ ስህተት እንደነበር ተናግሯል።ፈርዲናንድ በሰጠው አስተያየት ተጫዋቹ የሚያደርጋቸው ነገሮች በሙሉ በጣም ውጤታማ ናቸው። እርሱ ምርጥ እና ድንቅ ተጫዋች ነው፤ ማንችስተር ዩናይትድ ሊያስፈርመው ይገባ ነበር ብዬ ካሰብኳቸው ተጫዋቾች አንዱ ነው» ሲል ገልጿል።ኮንሳ ወደ ሰሜን ለንደን ያደረገውን ዝውውር ተከትሎ በአርሰናል ተከላካይ መስመር ላይ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ ይገኛል።👉ጋቪ ከባርሴሎና እንደማይለቅ ወኪሉ ተናገረ።የስፔኑ አማካይ ጋቪ ከባርሴሎና ሊለቅ ነው በሚል የሚናፈሱ የዝውውር ወሬዎችን ወኪሉ አስተባብሏል።ወኪሉ ደ ላ ፔኛ ተጫዋቹን በተመለከተ ከማንም ክለብ ጋር ንግግር አለማድረጉን በመግለጽ “ከማንም ጋር አልተደራደርኩም፤ ጋቪ በባርሴሎና ይቆያል” ሲል የወጡትን ዘገባዎች ውድቅ አድርጓል።ተጫዋቹ በአሠልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ስር በቂ የመጫወት ዕድል ባለማግኘቱ እና በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ብዙ ጊዜ ባለመካተቱ ምክንያት በጥር የዝውውር መስኮት ክለቡን ሊለቅ ይችላል የሚሉ ዘገባዎች ተሰራጭተው ነበር።በተለይም የጣሊያኑ ናፖሊ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ እንደነበር ቢዘገብም ተጫዋቹም ኾነ ወኪሉ ግን በባርሴሎና ቆይታቸውን ለመቀጠል ወስነዋል።👉ጁድ ቤሊንግሃም የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግብ ብዛቱን 16 በማድረስ ከታላላቅ ተጫዋቾች ተርታ ተሰለፈ።የሪያል ማድሪዱ እንግሊዛዊ አማካይ ጁድ ቤሊንግሃም በሻምፒዮንስ ሊጉ ያስቆጠረውን የግብ ብዛት 16 ማድረሱን ተከትሎ የቀድሞ የቡድኑ ኮከብ ዳቪድ ቤካም እና ኬቪን ደ ብሮይን ካስመዘገቡት የግብ መጠን እኩል መኾን ችሏል።ቤሊንግሃም ገና በለጋ እድሜው በሻምፒዮንስ ሊጉ በታሪክ ከፍተኛ ግብ ባስቆጠሩ እንግሊዛውያን ተጫዋቾች ሰንጠረዥ ውስጥ 10ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ ከታላላቅ ተጫዋቾች ተራ ተሰልፏል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_27_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here