ትኩረት የሚፈልጉት ምንትዋቦች

0
19
ያለፈው የውድድር አመት በኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የምድቡ መሪ እስከ መሆን ደርሰው ነበር ፤ የፋሲል ከነማ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ ።
በመጨረሻ አካባቢ የጣሏቸው ነጥቦች ምክንያት ወደ ሚፈልጉት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሳያድጉ ቀርተዋል። ዘንደሮም እንዳለፈው አመት
ተፎካካሪ ለመሆን ፍላጎት አላቸው። ነገር ግን በስብስቡ ውስጥ የነበሩ አብዛኞቹ ተጫዋቾች በክፍያ ምክንያት ወደ ተሻለ ክለብ ሄደዋል ። በዚህ በሚፈልጉት ልክ ተጫዋች ባያገኙም ዝግጅታቸውን ማድረጋቸውን የቡድኑ አሰልጣኝ ተስፋሁን እሸቴ ፡፡ ክለቡ ካለፉት የውድድር አመት አንፃር
የተሻለውን ጊዜ ያሳለፈበት ያለፈው አመት ልክ ለመቀጠል የስብስብ ችግር አለበት ፡፡ በሐሆኑም ለተሳትፎ ቡድኑን ለመገንባት እንደ አዲስ ተጫዋቾችን ምልመላ አድርገው የክለብ ልምድ የሌላቸውን ልጆች ይዘዋል። አዳዲስ ተጫዋቾችን እና የጨዋታ ልምድ የሌላቸውን ታዳጊዎችን
በከፍተኛ ሊጉ ልምድ ካላቸው ክለቦች ጋር ተፎካክሮ ወደ ላይኛው የሊግ እርከን ለማደግ ከባድ ቢሆንም ለመፎካከር እንሞክራለን ብሏል የቡድኑ አሰልጣኝ ተስፋሁን እሸቴ። የፋሲልከነማ ሴቶች በኢትዩጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት እሁድ 8፡00 ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ
ጋር በሃዋሳ አርቴፌሻል ሜዳ ይጫዎታሉ፡፡
ዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here