ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ (ዶ.ር) እንዳሉት በአፍሪካ እግር ኳስ ላይ በርካታ እምቅ አቅም ያላቸው አፍሪካውያን ሴት ተጫዋቾች እና የስፖርት ወዳዶች አሉ። እነዚህን ሴቶች በሳይንሳዊ መንገድ በማሠልጠን እና ፕሮፌሽናል ደረጃ ላይ በማድረስ ሀገርን እንዲኹም አህጉሩን መጥቀም ይቻላል። ለዚህም ነው ካፍ ሴት እግር ኳስ አሠልጣኞች ላይ ኢንቨስት እያደረገ ያለው ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ሠልጣኞች ወደ ሥራው ሲሰማሩ ሌሎች ለእግር ኳስ ፍቅር ያላቸውን ታዳጊ ሴቶች በቀላሉ ወደ ሜዳ እንዲመጡ ያነሳሳሉ፤ በመኾኑም የሥልጠናው ፋይዳ ከፍተኛ እንደኾነም አስረድተዋል። በካፍ የእግር ኳስ የአሠልጣኝነት ሥልጠና ወስደው የተመረቁት ሴት ኮንጓዊያን 30 ሲኾኑ በሁለተኛው የሥልጠና መርሐ ግብርም በርካታ ሴቶች ለመሳተፍ መመዝገባቸውን ካፍ ኒውስ ዘግቧል።
ሥልጠናው በተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች እንደ አውሮፓ አቆጣጠር እስከ 2025 እንደሚቀጥልም የካፍ መረጃ ያመላክታል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!