የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሌሶቶ ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን ነገ ያካሂዳል።

0
284

ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገራት የወዳጅነት ጨዋታዎችን በሚቀጥሉት ቀናት ያካሂዳሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ባልተለመደ መልኩ በእነዚህ ቀናት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ያደርጋል። ቡድኑ ከሌሶቶ ጋር ሁለት ጨዋታዎችን ለማድረግ መርሐ ግብር ይዟል። የመጀመሪያው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ነገ ሐሙስ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሠልጣኝ ገብረ መድን ኀይሌ የሚመራ ሲኾን ለጨዋታው 26 ተጫዋቾችን አሠባስቦ ልምምድ ከጀመረ ቀናት ተቆጥረዋል። በቅርቡ ወደ ግብፅ ሊግ ያመራው አጥቂው አቤል ያለውም ቡድኑን መቀላቀሉን ስኮር ኢትዮጵያ አስነብቧል። የኢትዮጵያ እና ሌሶቶ ጨዋታ ነገ ሐሙስ 9 ሰዓት ይካሄዳል። ሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ እሑድ ይከናወናል።

ጨዋታዎቹ ውድድር ካስተናገደ ብዙ ጊዚያት ባስቆጠረው አዲስ አበባ ስታድየም እንደሚካሄዱም ታውቋል።

በአስማማው አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here