አጫጭር ስፖርታዊ መረጃዎች::

0
110
👉የክርስቲያኖ ሮናልዶ የበኩር ልጅ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጁኒየር ለመጀመሪያ ጊዜ ለፖርቹጋል ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተደረገለት።
ወጣቱ ተጫዋች ጥሪው የደረሰው ለሚመጣው የአውሮፓ ሻምፒዮና ማጣሪያ ጨዋታዎች ሲኾን፣ ይህም ለሮናልዶ ቤተሰብ እና ለተጫዋቹ እግር ኳስ ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ኾኖ ተመዝግቧል።
👉ዌስትሃም ዩናይትድ ዋና አሰልጣኙን ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶን ከኀላፊነታቸው ማሰናበቱን በይፋ አረጋግጧል። ቡድኑ በቻምፒየንሺፑ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ለክለቡ አሠልጣኝ እስኪመደብ በጊዜያዊነት ማርክ ኖብል እና ስቲቭ ፖትስ ቡድኑን በመረከብ ለቀጣይ ጨዋታ ያዘጋጃሉ ነው የተባለው።
👉የሊቨርፑል አማካኝ ሪያን ግራቨንበርክ በተረከዙ ላይ በገጠመው የጉዳት ምክንያት ከፌነርባቼ ጋር ለሚደረገው የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ከሥብሥቡ ውጪ መኾኑን ክለቡ ይፋ አድርጓል።
ኔዘርላንዳዊው አማካኝ ቡድኑ ወደ ኢስታንቡል ከሚያደርገው ጉዞ ውጪ የኾነ ሲኾን ይህም ለሊቨርፑል አማካኝ ክፍል ተጨማሪ የጉዳት ጫና ፈጥሯል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here